የአይሻ II የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ ጀመረ፡-

የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜ ሽ ዕቅዳን አካል የሆው የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ፕሮጀክት ከአዲሰ አበባ በ700 ኪ.ሜ. እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 180 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኢትዮጵያ ሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በሽንሌ ዞን፣ ልዩ ስሙ አይሻ ወረዳ በተባለው ቦታ ላይ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክት የግንባታ ሥራውን ለማከናወን ጥር 06 ቀን 2008 ዓ.ም ዶንግ ፋንግ ኤሌክትሪክ ኢንተርናሽናል ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የኮንትራት ሥምምነት የተደረገ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ከመነሻውም የዲዛይን፣ የአፈር ጥናትና ምርመራ፣ የሃይድሮሎጂ፣ የማይክሮሳይቲንግ፣ እንዲሁም የከርሰ-ምድር ውሃ ቁፋሮና ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎች በማከናወን በባለፈው ዓመት የካቲት ወር 2009 ዓ.ም ሲሆን፤ የግንባታ ሂደቱን ለማስጀመር ወደ እንቅስቃሴ ተገብቷል፤

በአሁኑ ሰዓትም የካምፕ አጥር ስራ፣ ለጊዜያዊ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት መሬት የማስተካከልና የፋዉንደሽን ቁፋሮ፣ የቤት ስራ ግብዓት የሚሆኑ እቃዎችን ወደ ፕሮጀክቱ የማጓጓዝ ተግባራት በመከናወን ላይ የሚገኙ መሆኑንና ባደረግነው የሳይት ምልከታችን የተገነዘብን ሲሆን፤ የጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች የመገጣጠም ስራ ሲጠናቀቅ ወደ ዋናው የፕሮጀክት ግንባታ ሰራ በቅርቡ እንደሚጀመርም የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ታረቀኝ ቀለሙ ገልፀውልናል፡፡
ይህ የአይሻ II የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ቀደም ብለው ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ካሉት ከአዳማ I ፣ ከአሸጎዳ እና የአዳማ II የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች በተገኘ የዕውቀት፣ የቴክኖሎጅ እና የአሰራር ልምድ ተሞክሮ ጭምር በመታገዝ የሚገነባ በመሆኑ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎቻችን በምንገነባበት ጊዚያቶች በተለይ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ወዲህ ከተለያዩ ዕውቀትና ልምድ ካካበቱ የውጭ ሃገራት የስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ጋር በመገንባት በሚደረገው ሂደትም በየደረጃው ያሉ ሙያተኞቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር በመቅሰምና አሁን አሁን በዘርፉ የምንገነባቸውን ፐሮጀክቶችን በራስ የሰው ኃይል ወደ መገንባት እየተሸጋገርን ያለን መሆኑንና ከዚህም አኳያ ይህንን ፕሮጀክትም የማማከር ሥራውን የሚያከናውነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግ የስራ ክፍል አማካኝነት በመሆኑ በዚህ ፕሮጀክትም የበኩላችን አወንታዊ ሚና የምናበረክት መሆኑ ይታመናል፡፡

PHO 287በ

ይህ ፕሮጀክት እየተገነባ ያለበት የአካባቢው የንፋስ ፍጥነትም በአማካኝ 8.87 ሜ/ሰ ያህል እንደሚደርስና የፕሮጀክት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተከናውኖ በሙሉ አቅሙ ማመንጨት በሚበቃበት ወቅት 120 ሜጋ ዋት ያህል ኃይል ማመንጨት እንዲችል ተደርጎ እየተገነባ ያለ በተያያዘ ሁኔታም ዓመታዊ የኃይል ምርት አቅሙ 436.07 ጊጋ ዋት በሰዓት የሚደርስ መሆኑን፣ ፕሮጀክቱም 48 ተርባይኖች የሚገነቡና በተያያዘም እያንዳንዳቸው 2.5 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ተርባይኖች እንደሚኖሩት፣ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የግንባታ ወጭም 257,285,160 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሰባት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ሺ አንድ መቶ ስልሳ ) የአሜሪካን ዶላር ያህል መሆኑም ከፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መረጃው፡-
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
በውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተጠናከረ፤
ታህሳስ/2010 ዓ.ም.

ከፈለጉ...