Hydro Power Projects

         ከሆለታ-ደዴሳ-ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ድረስ የተዘረጋው ባለ 5ዐዐኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ግንባታ 99 በመቶ ተጠናቀቀ፡፡

 • እንደሚታወቀው ሁሉ የሃገራችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ የዕድገት እንቅስቃሴዎች በእጅጉ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚፈልጉ በመሆኑ ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ መንግሥታችንም ለኃይል ልማቱ ዘርፍ በሠጠው የላቀ ትኩረት እና ብሎም ሜጋ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፤
 • ከዚህም ጋር ተያይዞ በአምስት ዓመቱ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድና የትግበራ ዓመታት፤በማመነጨት አሁን ያለንን አቅም 2421 ሜጋዋት ያህል ሲሆን፤ ሩቅ በማይባል ጊዜያት ውስጥም ከዚህ በታች የተገለፁት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው በሙሉ አቅማቸው ማመንጨት በሚጀምሩበት ጊዜም 10ሺ ሜጋዋት ባለቤቶች የምንሆነ ሲሆን በGTP I ያልተጠናቀቁትን በGTP II ዕቅድ ጋር በማካታት 17,000 ሜጋዋት በላይ ለማመነጨት ሰፊ ዕቅድ ተይዞ ከፍተኛ ርብርብ በመደረግ ላይ ይገኛል፤ እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከልም በአሁን ሰዓት፡-
የፕሮጀክቱ ስም አሁን ያለውክንውን በመቶኛ ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ማመንጨት የሚችሉት ሜጋ ዋት መጠን
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 63% (6450 ሜጋዋት)
የገናሌ ዳዋ III 94% (254 ሜጋዋት)
ረጲ ከደረቅ ቆሻሻ 96% (50 ሜጋዋት)
አባ ሳሙኤል 96.96% (6.6 ሜጋዋት)
ባምዛ 4.7 (120.5 ሜጋዋት)
መልከሰዲ 27.5 (137.5 ሜጋዋት)
አሉቶ ላንጋኖ (70 ሜጋዋት) ከ24 ጉድጓዶች መካከልም የሁለቱ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራው በሶስት ፌዞች የሚከናወን ሲሆን፤ በመጀመሪያው ፌዝ ከሚከናወኑት መካከልም የሁለቱ ጉድጓዶች ቁፋሮና ሥራ 90በመቶ ያህል ሥራው ተከናውኗል፤

ያህል የግንባታ እንቅስቃሴዎቻቸው የተከናወነ ሲሆን፤ የዚሁ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ አካል የሆኑትና ያመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያስተላልፉ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና የማከፋፈያ ጣቢያዎችም እንዲሁ ግንባታቸው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

DSC03929

 • ስለሆነም የሃገራችን ዕድገት የወለደውና በአይነቱ ልዩና የመጀመሪያ የሆነው የሆለታ-ደዴሣ-ህዳሴ ባ500 ኪ.ቮ ጥምር ከፍተኛ የኤሌከትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያም የዕቅዱ አንዱ አካል ነው፡፡
 • የፕሮጀክቱ ግንባታ – በሰኔ 2005 ዓ.ም. ተጀመረ
 • ደብል ሰርኪዩቱ በመሀል ላይ 60 ሜት ተራርቆ ነው እየተገነባ ያለው፤
 • አጠቃላይ ርዝመት 619 ኪ.ሜ በእጥፍ ሲሆን በድምሩ 1,336 ኪ.ሜ (ከህዳሴ-ደዴሳ 344፣ ከደዴሳ – ሆለታ 275፣ ከሆለታ ሆለታ፣ ሰበታ እንዲሁም አቃቂ ባለ 400 ኪ.ቮ 98.2 ኪ.ሜ)
 • የታወር ብዛት – 500 = 2,764
 • 400 = 224

          2,988 (ስፓን 500 ሜትር በአመካኝ             

 • 2,222 (መሠረታቸው የተሰራ) ሙሉ በሙሉ የቆሙ ታወሮች = 1,324
 • የአንዱ ታወር ርዝመት 75 ሜትር (500)
 • የተፈጠረ ጊዜያዊ የሥራ ዕድል
  • ኢትዮጵያ = 4,500 (450 ሴቶች ናቸው)
  • ቻይና 2,000

     በድምር = 6,500 (ሠራተኞች)

 • በአሁኑ ጊዜም 99 በመቶ ያህል ተጠናቋል፤
 • እንዲሁም በተመሳሳይ የቮልቴጅ መጠንም አዲስ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ማለትም፡-

– ደዴሳ ባለ 500 ኪ.ቮ

– ሆለታ ባለ 500 ኪ.ቮ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፤

ከነዚህም ጋ ተያይዞ

– ሰበታ፣ ሱሉልታ እና አቃቂ ላይ ባለ 400 ኪ.ቮ የአቅም ማሳደግ ሥራም ተከናውኗል፤

 • የማስተላለፊያ መስመሩንም ሆነ የማከፋፈያ ጣቢያዎችን የገነባው ኮንትራክተር CET, (Chaina Electric Power Equipment Technology) የተባለ ኩባንያ ነው፤
 • የማስተላለፊያ መስመሩ ወጪ ብር 65 ቢሊዮን
 • የማከፋፈያ ጣቢያዎች ወጪ ደግሞ ብር 2 ቢሊዮን

ድምር…ብር 26.8 ቢሊዮን ያህል ነው፤

 • የገንዘቡም ምንጭ 85 በመቶ ከቻይና ኤግዚም ባንክ 15 በመቶ በሃገራችን የሚሸፈን ይሆናል፤
 • ይህን ፕሮጀክት ልዩ የሚያደርገው ባለ 500 ኪ.ቮ. የመጀመሪያው እና የሃገራችን ዕድገት የወለደው ነው፤

በመሆኑም 6ሺሜጋ ማመንጨት አቅም ያለው (በአፍሪካ 1ኛ፣ በዓለም 7ኛ ደረጃን) የሚይዘው የታላቁ የህዳሴ ግድባችን ኃይል ማመንጨት ሲጀምርም ወደ ተያያዙት የኃይል ትስስር በማገናኘት ጥቅም ላይ መዋል ያስችላል፤

 • በሌላ በኩል ደግሞ ከህዳሴ – በለስ 240 ኪ.ሜ ያህል ባለ 400 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር በተመሳሳይ የቮልት መጠን ማከፍፈያ ጣቢያም ሙሉ በሙሉ ተገንብቶ ኃይል ባመነጨበት ፍጥነት ጥቅም ላይ ለማዋል የማመንጨቱን ሂደት እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡
 • በአሁኑ ጊዜም የሃገራችን የኢኮኖሚ አቅም እያደገ በመምጣቱም የኃይል ማመንጫዎችን፣ የኃይል ማስተላለፊያዎችን እንዲሁም የማከፋፈያ ጣቢያዎችን ጎን ለጎን በአንዴ መገንባት እና ኃይልም ባመነጨበት ፍጥነት ጥቅም ላይ ለማዋል ምቹ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ተችሏል፡፡
 • መስመሩ ከሠበታ ከሱሉልታ እና ከአቃቂ ነባር ባለ 400 ኪ.ቮ መስመሮች ጋር የሙከራ ፍተሻ ሥራ በአጥጋቢ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡

DSC03973

በአጠቃላይ፡-

 • የስራ ተቋራጩ በደንብ የተደራጀ እና በጥራትም እና ስራውንም በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚፈልግ በመሆኑ ይህንንም በተግባር እያረጋገጠ በመሆኑ ስራው በታቀደለት ጊዜ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡

ምስክር ነጋሽ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የውጭ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር

ጥር /2008 ዓ.ም.

ድሬዳዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

DSC02966

የቆቃ-ሁርሶ-ድሬዳዋ ባለ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የሀገሪቱን ምስራቃዊ ክፍሎች ያካለለና ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ያለው ፕሮጀክት ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት ከቆቃ ተነስቶ ሁርሶ ከዚያም መዳረሻውን ድሬዳዋ ከተማ ካደረገውና 338 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውን ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርን ጨምሮ የሁርሶ ባለ 230 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያንና የአዋሽ ባለ 132 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክቶችን ያጠቃልላል፡፡

በ2005 ዓ.ም የመጀመሪያ ወራቶች የግንባታ ስራው የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ስራው 99 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የሲቪል፣የኤሌክትሮ ሜካኒካል እንዲሁም የኮሚሽኒንግ ስራዎችን በማከናወን ኢነርጃይዝ ለማድረግና አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቆ ከኤል ዲ ሲ የይሁንታ ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

ከዋና ዋና ስራዎች መካከል በሶማሌ ክልል፣በሽንሌ ዞን በየረር ወረዳ የሚገኘው የሁርሶ ባለ 230 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡

ይህንን የኃይል ማከፋፈያ መስመር ግንባታ ለማጠናቀቅ ባለፉት አራት ዓመታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

የቦታ መረጣ፣የቦታ ማፅዳት፣የመሰረት ቁፋሮ፣የ4 ሻንት ሪያክተርና የ3 ትራንስፎርመሮች ተከላ ከተከናዎኑ ስራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡የቆቃ-ሁርሶ-ድሬዳዋ ባለ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የሀገሪቱን ምስራቃዊ ክፍሎች ያካለለና ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ያለው ፕሮጀክት ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክት ከቆቃ ተነስቶ ሁርሶ ከዚያም መዳረሻውን ድሬዳዋ ከተማ ካደረገውና 338 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውን ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርን ጨምሮ የሁርሶ ባለ 230 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያንና የአዋሽ ባለ 132 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክቶችን ያጠቃልላል፡፡
በ2005 ዓ.ም የመጀመሪያ ወራቶች የግንባታ ስራው የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ስራው 99 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የሲቪል፣የኤሌክትሮ ሜካኒካል እንዲሁም የኮሚሽኒንግ ስራዎችን በማከናወን ኢነርጃይዝ ለማድረግና አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቆ ከኤል ዲ ሲ የይሁንታ ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
ከዋና ዋና ስራዎች መካከል በሶማሌ ክልል፣በሽንሌ ዞን በየረር ወረዳ የሚገኘው የሁርሶ ባለ 230 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡
ይህንን የኃይል ማከፋፈያ መስመር ግንባታ ለማጠናቀቅ ባለፉት አራት ዓመታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
የቦታ መረጣ፣የቦታ ማፅዳት፣የመሰረት ቁፋሮ፣የ4 ሻንት ሪያክተርና የ3 ትራንስፎርመሮች ተከላ ከተከናዎኑ ስራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

DSC03048ይህ የኃይል ማከፋፈያ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን አራት ተጠባባቂ ቤዮችን ጨምሮ 22 ቤይ፣አራት ሻንት ሪያክተርና ሶስት ግዙፍ ትራንስፎርመሮችን በውስጡ ያቀፈ ነው፡፡

ከትራንስፎርመሮቹ መካከል ሁለቱ አውቶ ትራንስፎርመሮች ሲሆኑ 230 ኪ.ቮ ወደ 133 ኪ.ቮ ዝቅ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው፡፡ ቀሪው አንድ ትራንስፎርመር ደግሞ የኃይል ትራንስፎርመር ሲሆን 132 ኪሎ ቮልትን ወደ 33 እና 15 ኪ.ቮ ለመቀየር የሚያገለግል መሆኑን የሳይቱ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ የሆኑት አቶ አኑዋር ሙሀመድ ገልፀውልናል፡፡

በተጨማሪም ለኃይል ማከፋፈያው የጀርባ አጥንት ሆነው የሚያገለግሉት የኮንትሮል ፓነል፣ፕሮቴክሽን ፓነል እንዲሁም የሞዛይክ ፓነል ስራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን የሰራተኞች መኖሪያ ቤቶችና የቢሮ ግንባታዎችም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ የኃይል ማከፋፈያ መስመር ባለ 230 ኪ.ቮ አንድ ገቢና ሁለት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን ለኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚዘረጋው የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመርም ከዚሁ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የሚነሱ መሆናቸውን የገለፁልን ደግሞ የሳይቱ የሲቪል ስራዎች መሐንዲስ አቶ ታምሩ ባቱ ናቸው፡፡

ይህ የኃይል ማከፋፈያ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን አራት ተጠባባቂ ቤዮችን ጨምሮ 22 ቤይ፣አራት ሻንት ሪያክተርና ሶስት ግዙፍ ትራንስፎርመሮችን በውስጡ ያቀፈ ነው፡፡

ከትራንስፎርመሮቹ መካከል ሁለቱ አውቶ ትራንስፎርመሮች ሲሆኑ 230 ኪ.ቮ ወደ 133 ኪ.ቮ ዝቅ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው፡፡ ቀሪው አንድ ትራንስፎርመር ደግሞ የኃይል ትራንስፎርመር ሲሆን 132 ኪሎ ቮልትን ወደ 33 እና 15 ኪ.ቮ ለመቀየር የሚያገለግል መሆኑን የሳይቱ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ የሆኑት አቶ አኑዋር ሙሀመድ ገልፀውልናል፡፡

በተጨማሪም ለኃይል ማከፋፈያው የጀርባ አጥንት ሆነው የሚያገለግሉት የኮንትሮል ፓነል፣ፕሮቴክሽን ፓነል እንዲሁም የሞዛይክ ፓነል ስራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን የሰራተኞች መኖሪያ ቤቶችና የቢሮ ግንባታዎችም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ የኃይል ማከፋፈያ መስመር ባለ 230 ኪ.ቮ አንድ ገቢና ሁለት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን ለኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚዘረጋው የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመርም ከዚሁ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የሚነሱ መሆናቸውን የገለፁልን ደግሞ የሳይቱ የሲቪል ስራዎች መሐንዲስ አቶ ታምሩ ባቱ ናቸው፡፡ይህ የኃይል ማከፋፈያ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን አራት ተጠባባቂ ቤዮችን ጨምሮ 22 ቤይ፣አራት ሻንት ሪያክተርና ሶስት ግዙፍ ትራንስፎርመሮችን በውስጡ ያቀፈ ነው፡፡
ከትራንስፎርመሮቹ መካከል ሁለቱ አውቶ ትራንስፎርመሮች ሲሆኑ 230 ኪ.ቮ ወደ 133 ኪ.ቮ ዝቅ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው፡፡ ቀሪው አንድ ትራንስፎርመር ደግሞ የኃይል ትራንስፎርመር ሲሆን 132 ኪሎ ቮልትን ወደ 33 እና 15 ኪ.ቮ ለመቀየር የሚያገለግል መሆኑን የሳይቱ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ የሆኑት አቶ አኑዋር ሙሀመድ ገልፀውልናል፡፡
በተጨማሪም ለኃይል ማከፋፈያው የጀርባ አጥንት ሆነው የሚያገለግሉት የኮንትሮል ፓነል፣ፕሮቴክሽን ፓነል እንዲሁም የሞዛይክ ፓነል ስራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን የሰራተኞች መኖሪያ ቤቶችና የቢሮ ግንባታዎችም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
ይህ የኃይል ማከፋፈያ መስመር ባለ 230 ኪ.ቮ አንድ ገቢና ሁለት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን ለኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚዘረጋው የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመርም ከዚሁ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የሚነሱ መሆናቸውን የገለፁልን ደግሞ የሳይቱ የሲቪል ስራዎች መሐንዲስ አቶ ታምሩ ባቱ ናቸው፡፡

DSC03045በሌላ በኩል 338 ኪ.ሜ የሚያካልለውና የግንባታ ስራው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው የቆቃ-ሁርሶ-ድሬዳዋ ባለ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ይገኝበታል፡፡

የታወር ጉድጓድ ቁፋሮ፣የታወር መሰረት ስራ፣የታወር ተከላና ገመድ ዝርጋታ ስራዎች በዚህ ፕሮጀክት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት የ790 ታወሮች ተከላና የኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታ ፣የኮሚሽኒንግ እንዲሁም አጠቃላይ ስራውን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተክለሐይማኖት ነግረውናል፡፡

እነዚህ ፕሮጀክቶች ለምስራቁ የሀገሪቱ ክፍሎች ብሎም ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በማቅረብ አህጉራዊ ትስስሩን ይበልጥ የሚያሳልጡት መሆኑን የፕሮጀክቶች ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዮ ጥላየ አብራርተዋል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ በምስራቁ ክፍል ለሚገኙ ለድሬዳዋ፣ሀረር፣ጅግጅጋ እንዲሁም ለሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች በቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ረገድ የማይተካ ሚና ይኖራቸዋል፡፡

ሁለተኛ መንግስት ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በሚያደርገው የህዳሴ ጉዞ ውስጥ ካቀዳቸው የኢንዱስትሪ መንደሮች መካክል የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ መንደር አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ይህ ፕሮጀክት ለዚህ ኢንዱስትሪ መንደር ኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርብ በመሆኑ ጠቀሜታውን ይበልጥ ያጎላዋል፡፡

ሶስተኛ በመገንባት ላይ ላለው ለኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር የሚቀርበው ከዚሁ ፕሮጀክት በመሆኑ ተፈላጊነቱነን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡

የመጨረሻውና ዋነኛው ጠቀሜታው ደግሞ ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት ለሚደረገው የኤሌክትሪክ ኃይል እንደ ዋና ምሰሶ ሆኖ የሚያገለግለው የሁርሶ የኃይል ማከፋፈያ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በመሸጥ አቅዳ እየተንቀሳቀሰች ያለውን ሰፊና ግዙፍ እቅድ ከማሳካት አንፃር የዚህ ፕሮጀክት ወሳኝነት የማያጠራጥር ሲሆን በተጨማሪም ሀገሪቱ በክፍለ አህጉሩ ያላትን ሁለንተናዊ ተሰሚነት በእጅጉ እንደሚያሳድግ ያታመናል፡፡

በሌላ በኩል 338 ኪ.ሜ የሚያካልለውና የግንባታ ስራው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው የቆቃ-ሁርሶ-ድሬዳዋ ባለ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ይገኝበታል፡፡

የታወር ጉድጓድ ቁፋሮ፣የታወር መሰረት ስራ፣የታወር ተከላና ገመድ ዝርጋታ ስራዎች በዚህ ፕሮጀክት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት የ790 ታወሮች ተከላና የኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታ ፣የኮሚሽኒንግ እንዲሁም አጠቃላይ ስራውን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተክለሐይማኖት ነግረውናል፡፡

እነዚህ ፕሮጀክቶች ለምስራቁ የሀገሪቱ ክፍሎች ብሎም ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በማቅረብ አህጉራዊ ትስስሩን ይበልጥ የሚያሳልጡት መሆኑን የፕሮጀክቶች ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዮ ጥላየ አብራርተዋል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ በምስራቁ ክፍል ለሚገኙ ለድሬዳዋ፣ሀረር፣ጅግጅጋ እንዲሁም ለሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች በቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ረገድ የማይተካ ሚና ይኖራቸዋል፡፡

ሁለተኛ መንግስት ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በሚያደርገው የህዳሴ ጉዞ ውስጥ ካቀዳቸው የኢንዱስትሪ መንደሮች መካክል የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ መንደር አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ይህ ፕሮጀክት ለዚህ ኢንዱስትሪ መንደር ኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርብ በመሆኑ ጠቀሜታውን ይበልጥ ያጎላዋል፡፡

ሶስተኛ በመገንባት ላይ ላለው ለኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር የሚቀርበው ከዚሁ ፕሮጀክት በመሆኑ ተፈላጊነቱነን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡

የመጨረሻውና ዋነኛው ጠቀሜታው ደግሞ ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት ለሚደረገው የኤሌክትሪክ ኃይል እንደ ዋና ምሰሶ ሆኖ የሚያገለግለው የሁርሶ የኃይል ማከፋፈያ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በመሸጥ አቅዳ እየተንቀሳቀሰች ያለውን ሰፊና ግዙፍ እቅድ ከማሳካት አንፃር የዚህ ፕሮጀክት ወሳኝነት የማያጠራጥር ሲሆን በተጨማሪም ሀገሪቱ በክፍለ አህጉሩ ያላትን ሁለንተናዊ ተሰሚነት በእጅጉ እንደሚያሳድግ ያታመናል፡፡በሌላ በኩል 338 ኪ.ሜ የሚያካልለውና የግንባታ ስራው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው የቆቃ-ሁርሶ-ድሬዳዋ ባለ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ይገኝበታል፡፡
የታወር ጉድጓድ ቁፋሮ፣የታወር መሰረት ስራ፣የታወር ተከላና ገመድ ዝርጋታ ስራዎች በዚህ ፕሮጀክት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት የ790 ታወሮች ተከላና የኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታ ፣የኮሚሽኒንግ እንዲሁም አጠቃላይ ስራውን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተክለሐይማኖት ነግረውናል፡፡
እነዚህ ፕሮጀክቶች ለምስራቁ የሀገሪቱ ክፍሎች ብሎም ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በማቅረብ አህጉራዊ ትስስሩን ይበልጥ የሚያሳልጡት መሆኑን የፕሮጀክቶች ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዮ ጥላየ አብራርተዋል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ በምስራቁ ክፍል ለሚገኙ ለድሬዳዋ፣ሀረር፣ጅግጅጋ እንዲሁም ለሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች በቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ረገድ የማይተካ ሚና ይኖራቸዋል፡፡
ሁለተኛ መንግስት ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በሚያደርገው የህዳሴ ጉዞ ውስጥ ካቀዳቸው የኢንዱስትሪ መንደሮች መካክል የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ መንደር አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ይህ ፕሮጀክት ለዚህ ኢንዱስትሪ መንደር ኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርብ በመሆኑ ጠቀሜታውን ይበልጥ ያጎላዋል፡፡
ሶስተኛ በመገንባት ላይ ላለው ለኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር የሚቀርበው ከዚሁ ፕሮጀክት በመሆኑ ተፈላጊነቱነን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡
የመጨረሻውና ዋነኛው ጠቀሜታው ደግሞ ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት ለሚደረገው የኤሌክትሪክ ኃይል እንደ ዋና ምሰሶ ሆኖ የሚያገለግለው የሁርሶ የኃይል ማከፋፈያ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ ለጎረቤት ሀገራት ኃይል በመሸጥ አቅዳ እየተንቀሳቀሰች ያለውን ሰፊና ግዙፍ እቅድ ከማሳካት አንፃር የዚህ ፕሮጀክት ወሳኝነት የማያጠራጥር ሲሆን በተጨማሪም ሀገሪቱ በክፍለ አህጉሩ ያላትን ሁለንተናዊ ተሰሚነት በእጅጉ እንደሚያሳድግ ያታመናል፡፡

ፕሮጀክቱ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከሰራተኞች መካከል ያነጋገርነው ወጣት ሀሰን አህመድ ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በቀን ሰራተኝነት እየሰራ መሆኑና ከጊዜ ወደ ጊዜ ሙያውን በማሻሻል በአሁኑ ጊዜ ዋና አናፂ መሆን እንደቻለ ገልፆ ሙያውን ከማሻሻል ባሻገርም በሚያገኘው የተሻለ ገቢ እሱንና ቤተሰቡን በጥሩ ሁኔታ ማስተዳደር መቻሉን ተናግሯል፡፡

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 15,299,779.93 ዩሮ፣14,139,253.82 እንዲሁም 249,066,046 ብር ሲሆን የገንዘብ ምንጩም 85 በመቶ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ ብድር የተሸፈነ ሲሆን ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው፡፡

የሁርሶ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክትን ኮንትራት በመውሰድ እያከናወነ የሚገኘው ሲሚ (CIMY) የተሰኘው የስፔን ካምፓኒ ሲሆን ሀገር በቀሎቹ ሲግማ ኤሌክትሪክ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እንዲሁም መላ ኮንስትራክሽን የሲቪል ስራዎችን ሰብ ኮንትራት በመውሰድ ስራቸውን አከናውነዋል፡፡ እነዚህ ሀገር በቀል ድርጅቶች የክህሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማግኘት ችለዋል፡፡

የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ደግሞ ኢነርጎ ኢንቨስት የተባለው የቦሲኒያ ካምፓኒ ኮንትራት ወስዶ ስራውን ማከናወን ችሏል፡፡

የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ደግሞ ኢነርጎ ኢንቨስት የተባለው የቦሲኒያ ካምፓኒ ኮንትራት ወስዶ ስራውን ማከናወን ችሏል፡፡ፕሮጀክቱ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከሰራተኞች መካከል ያነጋገርነው ወጣት ሀሰን አህመድ ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በቀን ሰራተኝነት እየሰራ መሆኑና ከጊዜ ወደ ጊዜ ሙያውን በማሻሻል በአሁኑ ጊዜ ዋና አናፂ መሆን እንደቻለ ገልፆ ሙያውን ከማሻሻል ባሻገርም በሚያገኘው የተሻለ ገቢ እሱንና ቤተሰቡን በጥሩ ሁኔታ ማስተዳደር መቻሉን ተናግሯል፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 15,299,779.93 ዩሮ፣14,139,253.82 እንዲሁም 249,066,046 ብር ሲሆን የገንዘብ ምንጩም 85 በመቶ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ ብድር የተሸፈነ ሲሆን ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው፡፡
የሁርሶ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክትን ኮንትራት በመውሰድ እያከናወነ የሚገኘው ሲሚ (CIMY) የተሰኘው የስፔን ካምፓኒ ሲሆን ሀገር በቀሎቹ ሲግማ ኤሌክትሪክ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እንዲሁም መላ ኮንስትራክሽን የሲቪል ስራዎችን ሰብ ኮንትራት በመውሰድ ስራቸውን አከናውነዋል፡፡ እነዚህ ሀገር በቀል ድርጅቶች የክህሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማግኘት ችለዋል፡፡
የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ደግሞ ኢነርጎ ኢንቨስት የተባለው የቦሲኒያ ካምፓኒ ኮንትራት ወስዶ ስራውን ማከናወን ችሏል፡፡

የግንባታ ስራውን በተያዘለት ጊዜ በስታንዳርዱ መሰረት ለማጠናቀቅ በፕሮጀክቱ ተቋራጭ ሲሚ ካምፓኒ በኩል ከፍተኛ ችግር እንደነበር የተጠቆመ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታትም በየጊዜው ከተቋራጩ ስራ አስኪያጆች ጋር በመነጋገርና ችግሩን በማቃለል ፕሮጀክቱን ከጫፍ ማድረስ እንደተቻለ መገንዘብ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል የዚህ ፕሮጀክት አንዱ አካል የሆነውና በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዋሽ ወረዳ ከአዲስ አበባ 200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የአዋሽ ባለ 230/132 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት ስራ ሊጠናቀቅ የተቃረበ ሲሆን አጠቃላይ ስራዉም 95 በመቶ ደርሷል፡፡

የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የሲቪል ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በቀጣይ ሁለት ወራቶች በማጠናቀቅ በመጭው መጋቢት ወር አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፋውንዴሽን ቁፋሮና የአርማታ ስራ፣የሁለት ትራንስፎርመሮችና የአምስት ቤዮች ተከላ የቅድመ ኮሚሽኒንግና የኮሚሽኒንግ ስራዎች ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ይህ ፕሮጀክት አንድ ወጪና ሁለት ገቢ መስመሮች ይኖሩታል፡፡

የሀገሪቱን የኃይል ስርጭት ከማሳለጥ ባሻገር የአዋሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት ከሌሎች የኃይል ማከፋፈያዎች ጋር በቅርበት በመገናኘቱ የቮልቴጅ መጠንን በመቀነስ የኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃቀማችንን በእጅጉ እንደሚያሻሽለው ይታመናል፡፡

ፕሮጀክቱ ከ200 በላይ ለሚሆኑ የሀገሪቱ ዜጎችም ጊዜያዊ የስራ እድል ሊፈጥር ችሏል፡፡

ይህ ፕሮጀክት የቆቃ ሁርሶ ድሬዳዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና የሁርሶ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክቶች አንዱ አካል በመሆኑ ከላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለዚህ ፕሮጀክት የሚውል መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

DSC03034

የአዋሽ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክትን ኮንትራት በመውሰድ እያከናወነ የሚገኘው ሲሚ (CIMY) የተሰኘው የስፔን ካምፓኒ ሲሆን ሀገር በቀሎቹ ሲግማ ኤሌክትሪክ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እንዲሁም መላ ኮንስትራክሽን የሲቪል ስራዎችን ሰብ ኮንትራት በመውሰድ ስራቸውን አከናውነዋል፡፡ እነዚህ ሀገር በቀል ድርጅቶች ከስፔን ባለሙያዎች በተለይም በቅድመ ኮሚሽኒንግና በኮሚሽኒንግ ስራዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ሙያዊ ክህሎት ማግኘት እንደቻሉ የሲግማ ኤሌክትሪክ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ የሆኑት አቶ ባንሸቢ ክፍትየ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ሳይጠቀስ ሊታለፍ የማይገባው ሁርሶ በሚገኘው የኃይል ማስተላለፊያ ታወሮች ላይ ኢትዮ ቴሌኮም የራሱን ኔትወርክ በመዘርጋት የአካባቢውን ህዝብ የስልክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ሲሆን ይህም በተቋማት መካከል ያለውን የተቀናጀና ተመጋጋቢ የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን የሚያሳይ ነው፡፡

በመጨረሻም ሳይጠቀስ ሊታለፍ የማይገባው ሁርሶ በሚገኘው የኃይል ማስተላለፊያ ታወሮች ላይ ኢትዮ ቴሌኮም የራሱን ኔትወርክ በመዘርጋት የአካባቢውን ህዝብ የስልክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ሲሆን ይህም በተቋማት መካከል ያለውን የተቀናጀና ተመጋጋቢ የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን የሚያሳይ ነው፡፡የግንባታ ስራውን በተያዘለት ጊዜ በስታንዳርዱ መሰረት ለማጠናቀቅ በፕሮጀክቱ ተቋራጭ ሲሚ ካምፓኒ በኩል ከፍተኛ ችግር እንደነበር የተጠቆመ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታትም በየጊዜው ከተቋራጩ ስራ አስኪያጆች ጋር በመነጋገርና ችግሩን በማቃለል ፕሮጀክቱን ከጫፍ ማድረስ እንደተቻለ መገንዘብ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል የዚህ ፕሮጀክት አንዱ አካል የሆነውና በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዋሽ ወረዳ ከአዲስ አበባ 200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የአዋሽ ባለ 230/132 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት ስራ ሊጠናቀቅ የተቃረበ ሲሆን አጠቃላይ ስራዉም 95 በመቶ ደርሷል፡፡
የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የሲቪል ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በቀጣይ ሁለት ወራቶች በማጠናቀቅ በመጭው መጋቢት ወር አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የፋውንዴሽን ቁፋሮና የአርማታ ስራ፣የሁለት ትራንስፎርመሮችና የአምስት ቤዮች ተከላ የቅድመ ኮሚሽኒንግና የኮሚሽኒንግ ስራዎች ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ይህ ፕሮጀክት አንድ ወጪና ሁለት ገቢ መስመሮች ይኖሩታል፡፡
የሀገሪቱን የኃይል ስርጭት ከማሳለጥ ባሻገር የአዋሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት ከሌሎች የኃይል ማከፋፈያዎች ጋር በቅርበት በመገናኘቱ የቮልቴጅ መጠንን በመቀነስ የኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃቀማችንን በእጅጉ እንደሚያሻሽለው ይታመናል፡፡
ፕሮጀክቱ ከ200 በላይ ለሚሆኑ የሀገሪቱ ዜጎችም ጊዜያዊ የስራ እድል ሊፈጥር ችሏል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የቆቃ ሁርሶ ድሬዳዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና የሁርሶ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክቶች አንዱ አካል በመሆኑ ከላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለዚህ ፕሮጀክት የሚውል መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
የአዋሽ የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክትን ኮንትራት በመውሰድ እያከናወነ የሚገኘው ሲሚ (CIMY) የተሰኘው የስፔን ካምፓኒ ሲሆን ሀገር በቀሎቹ ሲግማ ኤሌክትሪክ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እንዲሁም መላ ኮንስትራክሽን የሲቪል ስራዎችን ሰብ ኮንትራት በመውሰድ ስራቸውን አከናውነዋል፡፡ እነዚህ ሀገር በቀል ድርጅቶች ከስፔን ባለሙያዎች በተለይም በቅድመ ኮሚሽኒንግና በኮሚሽኒንግ ስራዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ሙያዊ ክህሎት ማግኘት እንደቻሉ የሲግማ ኤሌክትሪክ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ የሆኑት አቶ ባንሸቢ ክፍትየ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ሳይጠቀስ ሊታለፍ የማይገባው ሁርሶ በሚገኘው የኃይል ማስተላለፊያ ታወሮች ላይ ኢትዮ ቴሌኮም የራሱን ኔትወርክ በመዘርጋት የአካባቢውን ህዝብ የስልክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ሲሆን ይህም በተቋማት መካከል ያለውን የተቀናጀና ተመጋጋቢ የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን የሚያሳይ ነው፡፡

DSC03004

የቆቃ-ሁርሶ-ድሬዳዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት

የጅግጅጋ ደጋሃቡር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የኃይል ዘርፉ ሌላው አዲስ ምዕራፍ

DSC03010

የግንባታ ስራው በግንቦት 2006 ዓ.ም የተጀመረውና ከሀገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ 786 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ጠረፍ አካባቢ የሚገኘው የጅግጅጋ ደጋሃቡር ባለ 132 ኪ.ቮ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ግንባታ 40 በመቶ ደርሷል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 402 ታወሮች ለመትከል የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ142 ታወሮች ተከላና የ88 የታወር መትከያ ጉድጓዶች የቁፋሮ ስራ ተከናውኗል፡፡

ይህ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር 171 ኪ.ሜ ያህል አጠቃላይ ርዝመት ሲኖረው እስከአሁንም 50 ኪ.ሜ የሚሸፍን የታወር ተከላ ስራ ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል፡፡

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አስራት እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ለሀገሪቱ በተለይም ለምስራቁ ክፍል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልፀው የእነዚህ ፕሮጀክቶች መገንባት በአሁኑ ጊዜ በመከናወን ላይ ያለውን ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እንደሆነ

አስረድተዋል፡፡

አስረድተዋል፡፡የግንባታ ስራው በግንቦት 2006 ዓ.ም የተጀመረውና ከሀገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ 786 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ጠረፍ አካባቢ የሚገኘው የጅግጅጋ ደጋሃቡር ባለ 132 ኪ.ቮ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ግንባታ 40 በመቶ ደርሷል፡፡
በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 402 ታወሮች ለመትከል የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ142 ታወሮች ተከላና የ88 የታወር መትከያ ጉድጓዶች የቁፋሮ ስራ ተከናውኗል፡፡
ይህ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር 171 ኪ.ሜ ያህል አጠቃላይ ርዝመት ሲኖረው እስከአሁንም 50 ኪ.ሜ የሚሸፍን የታወር ተከላ ስራ ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል፡፡
የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አስራት እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ለሀገሪቱ በተለይም ለምስራቁ ክፍል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልፀው የእነዚህ ፕሮጀክቶች መገንባት በአሁኑ ጊዜ በመከናወን ላይ ያለውን ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እንደሆነ
አስረድተዋል፡፡

DSC03017

ከዚህ ጎን ለጎን ባለ 132 ኪ.ቮ የደጋሀቡር የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት ግንባታም በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የኃይል ማከፋፈያ ቦታ መረጣና የማፅዳት ስራዎች፤የኃይል ማከፋፈያ የመሰረት ቁፍሮ፤የአርማታ ስራዎችና የሰራተኞች መኖሪያ ቤትና ቢሮዎች ግንባታ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ዋና ዋናወቹ ናቸው፡፡

በቀጣይም የትራንስፎርመርና የሻንት ሪያክተር ተከላን ጨምሮ የሌሎች የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የሲቪል ስራዎች የሚከናወኑ መሆኑን የፕሮጀክቱ መሐንዲስ አቶ አብዲ ኪያር ገልፀዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ለ78 የሀገሪቱ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ፕሮጀክቱን በጎበኘንበት ወቅት ሲሰራ ያገኘነው ወጣት አያሌው አበበ በዚህ ፕሮጀክት በተፈጠረለት የስራ እድል የራሱን ህይወት ከማሻሻል አልፎ በሚያገኘው ገቢ ወንድሙን እያስተማረ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡

ሌላዋ ያነጋገርናት ወ/ሮ ቀለሟ ታደሰ እንደገለፀችው ደግሞ በምታገኘው ገቢ ሁለት ልጆቿን እያስተማረች መሆኑን ገልፃልናለች፡፡

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 52 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 80 በመቶ የአረብ ባንክ አካል ከሆኑት ባዲያ (BADEA) ኦፊድ (OFID)ና ኤስ ኤፍ ዲ (SFD) በብድር በተገኘ ገንዘብ የሚሸፈን ሲሆን ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት                                      የሚሸፈን ነው፡፡

የፕሮጀክቱን ስራ ከሀገር አቀፍ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ኮንትራት በመውሰድ ግንባታውን በማከናወን ላይ የሚገኘው የራስ ኃይል የሆነው የኤሌክትሪክ ኃይል ኮንስትራክሽን ቢሮ ሲሆን ይህም ተቋማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፕሮጀክቶችን በራሱ የሰው ኃይል የመገንባት አቅሙን እያጎለበተ መምጣቱን ያሳያል፡፡ በቀጣም የኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም መገንባት እንድንችል ያለመ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ስራ በመጋቢት 2007 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እቅድ ቢቀመጥም በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሊጠናቀቅ አልተቻለም፡፡ ለፕሮጀክቱ ስራ መጓተትም በርካታ ምክንያቶች የሚጠቀሱ ሲሆን የእቃ አቅራቢ ድርጅቶች የግንባታ እቃዎችን በወቅቱ አለማቅረብ፤ የግንባታ እቃዎች ግዥ መጓተት በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አቶ ያሬድ አስረድተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ስራ በመጋቢት 2007 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እቅድ ቢቀመጥም በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሊጠናቀቅ አልተቻለም፡፡ ለፕሮጀክቱ ስራ መጓተትም በርካታ ምክንያቶች የሚጠቀሱ ሲሆን የእቃ አቅራቢ ድርጅቶች የግንባታ እቃዎችን በወቅቱ አለማቅረብ፤ የግንባታ እቃዎች ግዥ መጓተት በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አቶ ያሬድ አስረድተዋል፡፡ከዚህ ጎን ለጎን ባለ 132 ኪ.ቮ የደጋሀቡር የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት ግንባታም በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የኃይል ማከፋፈያ ቦታ መረጣና የማፅዳት ስራዎች፤የኃይል ማከፋፈያ የመሰረት ቁፍሮ፤የአርማታ ስራዎችና የሰራተኞች መኖሪያ ቤትና ቢሮዎች ግንባታ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ዋና ዋናወቹ ናቸው፡፡
በቀጣይም የትራንስፎርመርና የሻንት ሪያክተር ተከላን ጨምሮ የሌሎች የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የሲቪል ስራዎች የሚከናወኑ መሆኑን የፕሮጀክቱ መሐንዲስ አቶ አብዲ ኪያር ገልፀዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ለ78 የሀገሪቱ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ፕሮጀክቱን በጎበኘንበት ወቅት ሲሰራ ያገኘነው ወጣት አያሌው አበበ በዚህ ፕሮጀክት በተፈጠረለት የስራ እድል የራሱን ህይወት ከማሻሻል አልፎ በሚያገኘው ገቢ ወንድሙን እያስተማረ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡
ሌላዋ ያነጋገርናት ወ/ሮ ቀለሟ ታደሰ እንደገለፀችው ደግሞ በምታገኘው ገቢ ሁለት ልጆቿን እያስተማረች መሆኑን ገልፃልናለች፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 52 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 80 በመቶ የአረብ ባንክ አካል ከሆኑት ባዲያ (BADEA) ኦፊድ (OFID)ና ኤስ ኤፍ ዲ (SFD) በብድር በተገኘ ገንዘብ የሚሸፈን ሲሆን ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡
የፕሮጀክቱን ስራ ከሀገር አቀፍ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ኮንትራት በመውሰድ ግንባታውን በማከናወን ላይ የሚገኘው የራስ ኃይል የሆነው የኤሌክትሪክ ኃይል ኮንስትራክሽን ቢሮ ሲሆን ይህም ተቋማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፕሮጀክቶችን በራሱ የሰው ኃይል የመገንባት አቅሙን እያጎለበተ መምጣቱን ያሳያል፡፡ በቀጣም የኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም መገንባት እንድንችል ያለመ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ስራ በመጋቢት 2007 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እቅድ ቢቀመጥም በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሊጠናቀቅ አልተቻለም፡፡ ለፕሮጀክቱ ስራ መጓተትም በርካታ ምክንያቶች የሚጠቀሱ ሲሆን የእቃ አቅራቢ ድርጅቶች የግንባታ እቃዎችን በወቅቱ አለማቅረብ፤ የግንባታ እቃዎች ግዥ መጓተት በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አቶ ያሬድ አስረድተዋል፡፡

በተለይም የግዥ ስርዓት መጓተት ችግሮች በብዙ ፕሮጀክቶች እንደ ዋና ማነቆ ሆነው ይነሳሉ፡፡ ስለሆነም ዘመናዊና ፈጣን የግዢ ስርዓትን መዘርጋት ለነገ የማይባል ወሳኝ ስራ መሆን እንደሚገባው ሳንጠቁም አናልፍም፡፡

በተለይም የግዥ ስርዓት መጓተት ችግሮች በብዙ ፕሮጀክቶች እንደ ዋና ማነቆ ሆነው ይነሳሉ፡፡ ስለሆነም ዘመናዊና ፈጣን የግዢ ስርዓትን መዘርጋት ለነገ የማይባል ወሳኝ ስራ መሆን እንደሚገባው ሳንጠቁም አናልፍም፡፡በተለይም የግዥ ስርዓት መጓተት ችግሮች በብዙ ፕሮጀክቶች እንደ ዋና ማነቆ ሆነው ይነሳሉ፡፡ ስለሆነም ዘመናዊና ፈጣን የግዢ ስርዓትን መዘርጋት ለነገ የማይባል ወሳኝ ስራ መሆን እንደሚገባው ሳንጠቁም አናልፍም፡፡

DSC03008

 የጅግጅጋ ደጋሃቡር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት በግንባታ ላይ