የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከመጋቢት 2010 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2011 ዓ.ም ባከናወናቸው አበይት የለውጥ ተግባራት ላይ በራስ ሆቴል የፖናል ውይይት እያካሔደ ይገኛል፡፡


የፓናል ውይይቱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ እየመሩት ይገኛሉ፡፡

በፓናል ውይይቱ ከመጋቢት እስከ መጋቢት የተከናወኑ አበይት ተግባራት ላይ ገለጻ ያደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ሥራ አሰፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ባቱ ናቸው፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እና የሚዲያ ተቋማት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

መጋቢት 26/2011 ዓ.ም

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ም/ቤት ፅ/ቤት ከሚዲያ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

”የሀገራችን ሚዲያ ለሀገሩ ግድብ“ በሚል መሪ ቃል ዛሬ በካፒታል ሆቴል በተዘጋጀው የግማሽ ቀን የምክክር መድረክ ላይ ግድቡ ከተጀመረ አንስቶ በነበረው ጊዜ ሚዲያዎች ያበረከቱት አስተዋጾ እና የነበሩባቸው ክፍተቶችን በመለየት ከተለያየ ሚዲያ ለመጡ ጋዜጠኞች  ገለጻ ተደርጓል፡፡

Continue Reading

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ የማስጀመር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

የህንፃ ግንባታውን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ እና በኢትዮጵያ የሲ.ጂ.ሲ.ኦ.ሲ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ጋኦ ሊ (Gao Lei) ናቸው፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር አብርሃም በላይ ተቋሙ ከተለያዩ የኃይል አማራጮች ኤሌክትሪክ በማመንጨት፣ በማስተላለፍ እና በማከፋፈል የሃገሪቱን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

Continue Reading

የገናሌ ዳዋ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመጫ ግድብ እየተጠናቀቀ መሆኑን ተከትሎ ውሃ የመያዝሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

የገናሌ ዳዋ III የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በይፋ ውሃ መያዝ ጀመረ፡፡

ውሃ በመያዝሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋናሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ ከፕሮጀክቱ አካባቢ በልማት ምክንያት ለሚነሱ ወገኖች የሚከፈል የካሳ ክፍያ በመዘግየቱ ምክንያት ግድቡ ውሃ መያዝ ከነበረበት ጊዜ እንዲዘገይ በእንዳደረገው ጠቁመዋል፡፡

በአካባቢው የሀገር ሽማሌዎች፣የሃይማኖት መሪዎች፣የቀበሌ፣የወረዳ፣የዞን እና የክልል መስተዳድር አካላት ከፍተኛ ትብብር የነበሩ ችግሮች ተፈተው ፕሮጀክቱ ውሃ የመያዝ ደረጃ ላይ ደርሷል ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ይሁን እንጂ ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው እንደ ወንዙ የፍሰት መጠን ከስድስት ወር በኃላ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ቀሪ ሥራዎች ተጠናቀው ኃይል ማመንጨት ሲጀምር የአካባቢውን ማህበረሰብ በማደራጀት በዓሳ እርባታ እና በቱሪዝም ዘርፍ ተሰማርተው የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ከሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

Continue Reading

ሃዘን መግለጫ

ትናንት መጋቢት 1/2011 ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ የነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737 ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ 149 ተሳፋሪዎችና 8 የበረራ ሰራተኞች በሙሉ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች በሙሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ይመኛል፡፡

 

የኢትዮጵያኤሌክትሪክኃይል የፋይናንስ ችግሮች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን የሒሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን አስታወቀ


የተቋሙን የፋይናንስ አሰራር ኦዲት ሲያደርግ የቆየው የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኦዲት ምርመራ ውጤት ከመጠነኛ የፋይናንስ አሰራርች ግሮች በቀር ጤናማ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

የተቋሙ የፋይናንስ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመረ አሰፋ እንደ ገለፁት ተቋሙ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሳይነጠል ጀምሮ ለኦዲት ሥራ አስተማማኝነት የሌለው ፣አጠራጣሪና ያልተሟላ ሂሳብ ሰነድ ያለው በመሆኑ በየዓመቱ የኦዲት አስተያየት  ይቀርብበት ነበር፡፡

ይሁንና ተቋሙ የሚሰጡትን የፋይናንስ አስተያየቶች ከፕሮጀክት ጽ/ቤቶች ጀምሮ እስከ ዋናመ/ቤት ድረስ በማረም፣መረጃ በማሟላትና የውስጥ ኦዲትን በማጠናከር አሰራሮቹን ማሻሻሉን ገልፀዋል፡፡

እንደ አቶ ደመረ ገለፃ የፋይናንስ አሰራሩ ጤናማ እየሆነ የመጣው ጠንካራ የቁጥጥርና የአሰራርሥርዓት በመዘርጋቱ ነው፡፡

Continue Reading

የቆቃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በሙሉ አቅሙ ኤሌክትሪክ እንዲያመነጭ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው

የቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ የማመንጫ ጀነሬተሮች አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው ምክንያት ጣቢያው በሙሉ አቅሙ እያመነጨ እንዳልሆነ የጣቢያው ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ ወ/ማሪያም ጥላዬ አስታወቁ፡፡

በአሁኑ ሰዓት የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ካሉት ሶስት ዩኒቶች ውስጥ ኤሌክትሪክ እያመነጨ የሚገኘው አንዱ ብቻ እንደሆነ ነው ኃላፊው የገለፁት፡፡

ግድቡ ከ60 ዓመት በላይ አገልግሎት እየሰጠ የቆዬ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በየጊዜው በሚያጋጥም የትራንስፎርመር ብልሽት እና በቂ የመለዋወጫ ዕቃዎች አለመኖር ምክንያት ማመንጨት ከሚችለው አቅም በታች እንዲያመነጭ ተፅዕኖ እንደፈጠሩበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

Continue Reading

የቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ የውሃ መውጫ ወለል የመሠረት ጥገና ሥራ ተጠናቀቀ

የቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የውሃ መውጫ ወለል መሠረት የሲቪል ሥራ ጥገና መጠናቀቁን የጀነሬሽን ኦፕሬሽን የሲቪል ጥገና ሥራዎች ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማ መንገሻ አስታወቁ፡፡

የጥገና ሥራውን ማከናወን ያስፈለገው የግድቡ የውሃ ከፍታ ሲጨምር በውሃ መልቀቂያ በሮች የሚለቀቀው ውሃ የግድቡን የታችኛውን ወለል በመቆፈር ሰፊና ጥልቅ ጉድጓድ በመፍጠሩ ምክንያት የግድቡን አስተማማኝነት ጥያቄ ውስጥ መክተቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የካቲት 2010 ዓ.ም ተጀምሮ ለፍፃሜ የበቃው የግድቡ የታችኛው የወለል ንጣፍ ግንባታ 2 ሺህ 250 ካሬ ሜትር እንደሚሸፍን አቶ ግርማ ገልፀዋል፡፡

Continue Reading

የጅግጅጋ - ደገሃቡር ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ዝግጁ እየሆነ ነው

ላለፈው አንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የጅግጅጋ - ደገሃቡር ከፍተኛ ባለ 132 ኪ ቮ. የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት የፍተሻና የሙከራ (Commissioning and Testing) ሥራ በመጠናቀቁ በቅርቡ ለአግልግሎት እንደሚበቃ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እና የማከፋፈያ ጣቢያ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ማናጀር አቶ ሰለሞን ኃይለጎርጊስ እንደገለጹት የኤክትሮ ሜካኒካል እና የሲቪል ግንባታ ሥራውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን ቢሮ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የሥራ ተቋራጭ ውል በመውሰድ አከናውኗል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የፍተሻና የሙከራ (Commissioning and Testing) ሥራ በመጠናቀቁ በቅርብ ቀናት ውሥጥ ሙለሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

Continue Reading

የአባ ሳሙኤል የውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ በዲዝል ጀኔሬተር ኃይል ማመንጨት እንደተጀመረ የታሪክ መዛግብት ያስረዳል፡፡ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአቃቂ ወረዳ አቃቂ ወንዝ ላይ ከአዲስ አበባ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመጀመሪያዉ የውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የሆነው የአባ ሳሙኤል የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ1931 ዓ.ም ግንባታው ተጀምሮ በ1933 ዓ.ም ነበር አገልግሎት መስጠት የጀመረው፡፡ በሦሥት ዩኒቶች 3.6 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የጀመረው ይህ የሃይል ማመንጫ ጣቢያ በ1946 ዓ.ም ማሻሻያ ተደርጎለት 3 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚችል አንድ ዩኒት በመጨመር አጠቃላይ የማመንጨት አቅሙን ወደ 6.6 ሜጋ ዋት ማሳደግ ተችሏል፡፡

Continue Reading

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮንትራት ሥምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ፓዎር ቻይና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር (Hydraulic Steel Structure) ግንባታ ለማከናወን ተስማሙ፡፡ የኮንትራት ሥምምነቱ የተደረገው የውሃ መቀበያ አሸንዳዎችን እና የመቆጣጠሪያ በሮችን እንዲሁም የአስራ አንድ የኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን የዲዛይን፣ የአቅርቦት፣ የገጠማ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ሥራዎችን ለማከናወን እንደሆነ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጅነር አብርሃም በላይ እና በኢትዮጵያ የፓዎር ቻይና ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ቲያን (Tian) ናቸው፡፡ ዶ/ር ኢንጅነር አብርሃም በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የህዝብ አሻራ ያረፈበት ሃገራዊ ፕሮጀክት በመሆኑ ሥምምነቱ ኃይል ማመንጫውን ዕውን ለማድረግ የተጀመሩትን አበረታች እንቅስቃሴዎች የሚያግዝ ነው፡፡ ሥራ ተቋራጩ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ግንባታውን አጠናቆ እንዲያስረክብ ከመቼውም ጊዜ በላይ የድጋፍ እና ክትትል ሥራዎች ይሰራሉም ብለዋል፡፡

Continue Reading

የባህርዳር 2፣ወልዲያ 2፣ ኮምቦልቻ2 እና ኮምቦልቻ 3 ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 402 ነጥብ 06 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ውስጥም 381.89 ኪሎ ሜትር ባለ 400 ኪሎ ቮልት ድርብ ሰርኪዩት ተሸካሚ ሲሆን 20.67 ኪሎ ሜትሩ ደግሞ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ድርብ ሰርኪዩት ተሸካሚ እንደሆነ የፕሮጀክት ቢሮው ተወካይ ስራ አስኪያጅ አቶ በለጠ ተሻለ ገልጸዋል፡፡ የፕሮጀክቱን ግንባታ የቻይናው ሻንጋይ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን (SHANGHAI ELECTRIC GROUP CO. LTD) እና ታታ ፕሮጀክትስ ሊሚትድ(TATA PROJECTS LTD) የተሰኘው የህንዱ ኩባንያ በስራ ተቋራጭነት በማከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን የማማከር ስራዉን ደግሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ቢሮ እያከናወነው ይገኛል፡፡ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ ከ5 ቢሊዬን ብር በላይ ሲሆን ይህም ከቻይና እና ከህንድ ኤግዚም ባንኮች በተገኘ ብድር እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን እንደሆነ ፕሮጀክት ቢሮው ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ 900 ምሰሶዎች የሚኖሩት ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ406 የምሰሶ መትከያ የቁፋሮና የመሰረት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡ የምሰሶ ተከላ ስራ ለመጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም አቶ በለጠ ገልፀዋል፡፡

Continue Reading

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራዎችን በአዲስ ኃይል ወደቀድሞ ፍጥነት ለመመለስ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራዎችን በአዲስ ኃይል ወደቀድሞ ፍጥነት ለመመለስ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ በዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም በላይ የተመራ የልዑካን ቡድን የግድቡን የሲቪልና የብረታብረት ስራዎች ጎብኝቷል፡፡ የግንባታው አማካሪዎች ትራክትቤል ኢንጂነሪንግና ኤልክ ኤሌክትሮ ኮንሰልት ተወካዮች እንደገለፁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ለታዩት ችግሮች ቴክኒካዊ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው። ቀደም ሲል የተጀመሩና የተከናወኑ ከብረታብረት ጋር የተያያዙ ስራዎች ከ90 በመቶ በላይ ፍተሻ ተደርጎ ችግሮቹን ለማረም የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውም ተገልጻል። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደተናገሩት የግድቡ የግንባታ ስራዎች መነቃቃት እየታየባቸው ነው። በመሆኑም የተለያዩ ሂደቶችን ማለፍ የማይጠይቁ የግንባታ ስራዎች በፍጥነት እንዲከናወኑ ሚኒስትሩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም በላይ በበኩላቸው የግድቡ ግንባታ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት ለማረምና ጉድለቱን ለማካካስ ተቋማቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የግድቡን ግንባታ ለማፋጠን ቀደም ሲል ከብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር በንዑስ ተቋራጭነት ለመስራት ውል የነበራቸው ተቋራጮች መካከል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከጂ ኢ ኃይድሮ ፍራንስ ጋር ውል ተፈራርሟል፡፡

ዋና አድራሻ

ኢኤኃ
ስ.ቁ:- +251-111-580598 ፣ +251-111-580631
ፋክስ:- +251-111-580528
ፖስታ ሳ.ቁ።- 15881, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ
ኢሜል፡- This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ፌስቡክ፡- www.facebook.com/eepgov
ለበለጠ መረጃ

ክልልላዊ መሥሪያ ቤቶች

ስለ ኢኤኃ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መብራት ኃይል ባለሥልጣን (በቀድሞ የእንግሊዝኛ ምዕፃሩ EELPA) በ1948 ዓ.ም. የተመሰረተ ሲሆን የአወቃቀር ማሻሻያ በማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን (EEPCo) የሚል ስያሜ ያዘ፡፡ ኮርፖሬሽኑ እንደገና በሁለት ተቋማት ተከፍሎ በመደራጀት የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ሃይል (EEP) እና ኤሌክትሪክ አግልግሎት (EEU) ተብሏል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ