• የቆቃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በሙሉ አቅሙ ኤሌክትሪክ እንዲያመነጭ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው

  የቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ የማመንጫ ጀነሬተሮች አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው ምክንያት ጣቢያው በሙሉ አቅሙ እያመነጨ እንዳልሆነ የጣቢያው ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ ወ/ማሪያም ጥላዬ አስታወቁ፡፡

  በአሁኑ ሰዓት የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ካሉት ሶስት ዩኒቶች ውስጥ ኤሌክትሪክ እያመነጨ የሚገኘው አንዱ ብቻ እንደሆነ ነው ኃላፊው የገለፁት፡፡

  ግድቡ ከ60 ዓመት በላይ አገልግሎት እየሰጠ የቆዬ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በየጊዜው በሚያጋጥም የትራንስፎርመር ብልሽት እና በቂ የመለዋወጫ ዕቃዎች አለመኖር ምክንያት ማመንጨት ከሚችለው አቅም በታች እንዲያመነጭ ተፅዕኖ እንደፈጠሩበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

 • የቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ የውሃ መውጫ ወለል የመሠረት ጥገና ሥራ ተጠናቀቀ

  የቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የውሃ መውጫ ወለል መሠረት የሲቪል ሥራ ጥገና መጠናቀቁን የጀነሬሽን ኦፕሬሽን የሲቪል ጥገና ሥራዎች ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማ መንገሻ አስታወቁ፡፡

  የጥገና ሥራውን ማከናወን ያስፈለገው የግድቡ የውሃ ከፍታ ሲጨምር በውሃ መልቀቂያ በሮች የሚለቀቀው ውሃ የግድቡን የታችኛውን ወለል በመቆፈር ሰፊና ጥልቅ ጉድጓድ በመፍጠሩ ምክንያት የግድቡን አስተማማኝነት ጥያቄ ውስጥ መክተቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

  የካቲት 2010 ዓ.ም ተጀምሮ ለፍፃሜ የበቃው የግድቡ የታችኛው የወለል ንጣፍ ግንባታ 2 ሺህ 250 ካሬ ሜትር እንደሚሸፍን አቶ ግርማ ገልፀዋል፡፡

 • የጅግጅጋ - ደገሃቡር ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ዝግጁ እየሆነ ነው

  ላለፈው አንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የጅግጅጋ - ደገሃቡር ከፍተኛ ባለ 132 ኪ ቮ. የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት የፍተሻና የሙከራ (Commissioning and Testing) ሥራ በመጠናቀቁ በቅርቡ ለአግልግሎት እንደሚበቃ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እና የማከፋፈያ ጣቢያ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ማናጀር አቶ ሰለሞን ኃይለጎርጊስ እንደገለጹት የኤክትሮ ሜካኒካል እና የሲቪል ግንባታ ሥራውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን ቢሮ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የሥራ ተቋራጭ ውል በመውሰድ አከናውኗል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የፍተሻና የሙከራ (Commissioning and Testing) ሥራ በመጠናቀቁ በቅርብ ቀናት ውሥጥ ሙለሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
 • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮንትራት ሥምምነት ተፈራረመ

  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ፓዎር ቻይና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር (Hydraulic Steel Structure) ግንባታ ለማከናወን ተስማሙ፡፡ የኮንትራት ሥምምነቱ የተደረገው የውሃ መቀበያ አሸንዳዎችን እና የመቆጣጠሪያ በሮችን እንዲሁም የአስራ አንድ የኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን የዲዛይን፣ የአቅርቦት፣ የገጠማ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ሥራዎችን ለማከናወን እንደሆነ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጅነር አብርሃም በላይ እና በኢትዮጵያ የፓዎር ቻይና ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ቲያን (Tian) ናቸው፡፡ ዶ/ር ኢንጅነር አብርሃም በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የህዝብ አሻራ ያረፈበት ሃገራዊ ፕሮጀክት በመሆኑ ሥምምነቱ ኃይል ማመንጫውን ዕውን ለማድረግ የተጀመሩትን አበረታች እንቅስቃሴዎች የሚያግዝ ነው፡፡ ሥራ ተቋራጩ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ግንባታውን አጠናቆ እንዲያስረክብ ከመቼውም ጊዜ በላይ የድጋፍ እና ክትትል ሥራዎች ይሰራሉም ብለዋል፡፡
 • የባህርዳር 2፣ወልዲያ 2፣ ኮምቦልቻ2 እና ኮምቦልቻ 3 ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

  የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 402 ነጥብ 06 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ውስጥም 381.89 ኪሎ ሜትር ባለ 400 ኪሎ ቮልት ድርብ ሰርኪዩት ተሸካሚ ሲሆን 20.67 ኪሎ ሜትሩ ደግሞ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ድርብ ሰርኪዩት ተሸካሚ እንደሆነ የፕሮጀክት ቢሮው ተወካይ ስራ አስኪያጅ አቶ በለጠ ተሻለ ገልጸዋል፡፡ የፕሮጀክቱን ግንባታ የቻይናው ሻንጋይ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን (SHANGHAI ELECTRIC GROUP CO. LTD) እና ታታ ፕሮጀክትስ ሊሚትድ(TATA PROJECTS LTD) የተሰኘው የህንዱ ኩባንያ በስራ ተቋራጭነት በማከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን የማማከር ስራዉን ደግሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ቢሮ እያከናወነው ይገኛል፡፡ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ ከ5 ቢሊዬን ብር በላይ ሲሆን ይህም ከቻይና እና ከህንድ ኤግዚም ባንኮች በተገኘ ብድር እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን እንደሆነ ፕሮጀክት ቢሮው ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ 900 ምሰሶዎች የሚኖሩት ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ406 የምሰሶ መትከያ የቁፋሮና የመሰረት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡ የምሰሶ ተከላ ስራ ለመጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም አቶ በለጠ ገልፀዋል፡፡

ዋና አድራሻ

EEP
Phone: +251 11 666 66 77
Fax: +251 11 666 66 78
P.O.Box 59, Addis Ababa, Ethiopia
Contacts

ክልልላዊ መሥሪያ ቤቶች

 • North
 • East
 • South
 • West

ስለ ኢኤኃ

EEP was established in 2013 by the Council of Ministers Regulation No.302/2013 and is responsible for generating, transmitting and wholesale electricity to be utilized nationwide as well as neighboring countries.
About EEP