Reppi Waste to Energy Project in Steady Progress

ከደረቅ ቆሻሻ (የረጲ) የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል

ደረቅ ቆሻሻ ከየዕለት ህይወታችን እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘና የሰው ልጅ ፍላጐትን ከማሟላትና ከመጠቀም ጋር በቅርብ የተቆራኘ ነው። ሰዎች ለዕለት ፍጆታቸው የሚጠቀሙባቸው ምግቦች የእነርሱ ማሸጊያዎች፣ የዕቃ መጠቅለያዎች፣ ቁርጥራጭ ወረቀቶች፣ የውሃ ማሸጊያ ፕላስቲኮች፣ ተረፈ ምርቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና በአጠቃላይ አገልግሎት ሰጥተው ያበቁ አልባሳትን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶች በቆሻሻነት ውስጥ እንደሚመደቡ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ሊቃውንቶች ያስረዳሉ።

በኢትዮጵያ የደረቅ ቆሻሻ አዋጅ 513/99 መሠረት ሁሉም የከተማ አስተዳደሮች የደረቅ ቆሻሻ አያያዛቸውን በተመለከተ በዕቅድ እንዲመሩና መሠረተ ልማት እንዲያመቻቹ የሚደነግግ ቢሆንም ህጉ ከወረቀት ባለፈ መሬት ላይ ወርዶ ሲሰራበት አይስተዋልም፤ ለዚህም እንደማሳያ የምንኖርባቸውን አካባቢዎች የፅዳት ሁኔታ መቃኘቱ በቂ ነው፡፡ ቆሻሻ በአግባቡ ካልተወገደ አካባቢን  በመበከል በሰውም ሆነ በእንስሳት ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው። በአግባቡ ከተከማቸና ከተያዘ ደግሞ መልሶ ጥቅም ላይ ሊውል ከመቻሉም በላይ ሀብት ሆኖ ለሌሎች ወገኖች የሥራ ዕድል መፍጠር ይችላል፡፡

Presentation2Presentation1                                                            የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ አሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት(Reppi Waste to Energy Project)

የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ልማቱ ዘርፍ የ25 ዓመቱን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጥናት ይፋ ባደረገበት ወቅት በሃገሪቱ ውስጥ በሚገኙ 35 ከተሞች ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል አቅም እንዳለ አስታውቋል፡፡ ከነዚህ 35 ከተሞች ውስጥ ደግሞ በአዲስ አበባ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚያስችል ግንባር ቀደም ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡

በተለምዶ ቆሼ ተብሎ የሚጠራው የረጲ አካባቢ በ37 ሔክታር መሬት ላይ ላለፉት 40 ዓመታት በየዕለቱ 900 ቶን ደረቅ ቆሻሻን ሲከመር የኖረ ቢሆንም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን ቆሻሻው አንዳችም ጊዜ ታክሞም ሆነ ወደሌላ ዓይነት ግብአትነት እንዲቀየር በከተማ አስተዳደሩም ሆነ በሚመለከታቸው አካላት ጥረት ተደርጎ እንደማያውቅ ጥናቶች ያመላክታሉ። 50 ሜጋ ዋት ማመንጨት እንዲችል ተደርጎ በመገንባት ላይ የሚገኘው የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአሁኑ ሰዓት በርካታ የሲቪል እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች እየተሰሩለት ይገኛል፡፡ እነዚህም የቆሻሻ ማጠራቀሚያው ክፍል (waste bank) ጣራ የማልበስ ግንባታ መጠናቀቁና ክሬን የመግጠም ሥራ መጀመሩ፣ የቆሻሻ ማቃጠያ ቤት (boiler hole) ላይ የጣራ ልባስ (steel structure) ሥራ
እየተከናወነ መሆኑ፣ ለኃይል ማመንጫ ቤት (power house) የሚያስፈልጉ ዕቃዎች ከወደብ ወደ ፕሮጀክቱ በመምጣት ላይ መሆናቸው፣ በዝቃጭ ማጣሪያ(leachat treatment)ክፍል ውስጥ የሲቪል ሥራ እየተሰራ መሆኑ፣ በፕሮጀክቱ ግቢ ውስጥ የመዳረሻ መንገዶች ግንባታ መጀመራቸው ዋና ዋናዎቹ የሲቪል እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል አበይት ክንውኖች እንደሆኑ የፕሮጀክቱ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለእንፋሎት አገልግሎት የሚውሉ እያንዳንዳቸው 180 ሜትር ጥልቀት ያላቸው ሶስት የከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮዎች በመከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ጉድጓድ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለግንባታ ሥራው የውሃ አቅርቦት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ 48 ሜትር ርዝመት ያላቸው ሁለት የጭስ ማስወጫ ቱቦዎች፣ 132 ኪ.ቮ መጠን ያለው አንድ ትራንስፎርመር፣ 10.5 ኪ.ቮ መጠን ያላቸው ሁለት ጄኔሬተሮች፣ አገልግሎት የጨረሰውን
የፈላ ውሃ የሚያቀዘቅዙ ሁለት የማቀዝቀዣ ማሽኖች፣ ሁለት የዘይት ታንከሮች (oil tankers) እና የእንፋሎት ተርባይኖቹን (steam turbines) አግድም ለማስቀመጥ የሚያስፈልጉ መደገፊያ መሣሪያዎች (lower case) የተከላ ሥራ መጠናቀቁን ከፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ አዲስ ባለ 132 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና ከመካኒሳ-ሰበታ ድረስ ከተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጋር የሚገናኝ 3 ኪ.ሜ የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ለመጀመር የዕቃ አቅርቦትና የካሳ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡

ይህ በአይነቱ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በዓመት ሊቀጣጠል የሚችል እስከ 437,500 ቶን ያህል ቆሻሻ የሚያስፈልገው ሲሆን፤ በዚህ የቶን መጠንም ከሁለት ዩኒቶች (25X2) በዓመት እስከ 185 ጌጋ ዋት በሰዓት ኢነርጂ ማግኘት እንደሚቻል ታውቋል፡፡ የእንፋሎት ተርባይን (steam turbines) የሚጠቀመው ይህ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ኤሌክትሪክ ለማመንጨት እስከ 530 ዲግሪ ሴንት ግሬድ የፈላ ውሃ የሚያስፈልገው ሲሆን፤ ይህም የሚሆነው ወደ ተርባይኑ የሚሔደውን እንፋሎት የግፊት መጠን ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በሰባት ሔክታር ላይ ያረፈው ይህ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአሁኑ ሰዓት አጠቃላይ የግንባታ አፈፃፀሙ 80.85 በመቶ መድረሱን ከፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን፤ ግንባታውን ሙሉ ለሙሉ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ፕሮጀክቱ ለ189 ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣87 የሚሆኑ የውጭ ሃገር ዜጎች በፕሮጀክቱ ሥራ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት መርዛማ ንጥረ ነገሮችን በማስወገድ የኃይል አቅርቦቱን ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ የሚደግፍ ከመሆኑም ባሻገር ከቆሻሻ ገበያ ገንዘብ በማመንጨት የአካባቢውን ነዋሪ ተጠቃሚ ለማድረግ ታልሞ እየተገነባ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በየዓመቱ ብዙ መጠን ያለው ካርቦንዳይኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ Bየሚያደርግ ሲሆን ይህም በዓለም የሙቀት መጨመርን ለመቀነስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታል። በተጨማሪም በአካባቢው ጤናማ የሆነ አየር እንዲኖር ከማድረጉም ባሻገር ለከተማዋ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ጉዞ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው ታምኖበታል፡፡ የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ መንግሥት በተሸፈነ 2.6 ቢሊዮን ብር እየተገነባ ይገኛል፡፡
አጠቃላይ ኮንትራቱን በመውሰድ የግንባታ ሥራውን እያከናወኑ የሚገኙት የእንግሊዙ ካምብሪጅ ኢንደስትሪስ ሊሚትድ እና የቻይናው ሲ.ኤን.ኢ.ኢ.ሲ ሊሚትድ (C.N.E.E.C Ltd) በአጋርነት (partnership) ሲሆን፤ በአማካሪነት ደግሞ የዴንማርኩ ራንቦል ኩባንያ መሆኑን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Reppi Waste to Energy Project in Steady Progress

Work on the Reppi Waste to Energy project (WtE) which is believed to be the first of its kind in Africa is in steady progress. The WtE project is being undertaken at place called
Reppi traditionally known by the name “Koshe” meaning a damping area of the urban waste in a total area of 37 hectares of land about 10km south-west of Addis Ababa. The initial production capacity of the project is 50 MW.

WtE is the process of generatin genergy, in the form of electricity from the primary treatment of dry waste. It is a form of energy recovery. Most Waste to Energy process produce electricity as well as heat directly through combustion or produce a combustible fuel commodity like methane, methanol, and synthetic fuel. Generally, waste is unwanted refuse materials from the community or house hold domestic or camp waste or from industrial activities (manufacturing, mining or agricultural). About 900 tons of dry waste has been damped in this area for the past 40 years. What is more, studies indicate that the waste had neither been treated nor tried to change to other qualitative inputs either by the City Administration council of Addis Ababa or any other concerned body. Major civil and electromechanical  works on the 50MW Reppi dry WtE project are in good progress.

In this light, roofing of the waste bank was accomplished. Where as, installation of crane and steel- structure of the boiler hole is under implementation. At the same time also, materials and equipment for the power house are being transported from the port to the project site. Civil works of the leach at treatment and accessible roads within the site area are being carried out. In addition, excavation of three ground water holes about a depth of 180m each and installation of two 48m long chimney pipes, 132kV transformer, two 10.5kV generators, two cooling machines of a tail race water, Two oil tankers, steam turbines, and erection of the lower casewere carried out.

Compensation and preconstruction preparations for erection and installation of 132kV substation and stretching a three kilometer transmission line and to link and creat an access towards the Mekanissa – Sabetta grid  network are being undertaken.
It is understood that about 437,500 tons of dry waste is needed to produce 185 Giga watt of energy per hour from two units (25×2) annually, 5300c steam is required to run the turbines and generate electricity.

The project is financed provided by 2.6 bilion birr by our Government of Ethiopia. At present, however 80.85 percent of work on the project that is being built on seven hactars of land has been carried out.
By this project for 189 Ethiopians and 87 expatriates are deployed in the project.

The WtE plant is believed to play a great role for reduction of carbondioxide from the atmosphere and plays its due share for the betterment of the environment in its vicinity.

 

ከፈለጉ...